ደቡብ አፍሪካ ያለዉ የኮካ ኮላ ኩባንያ ደንበኞቹ አማራጮች እንዲያገኙ ይሰራል።

19-10-2022

የኮካ ኮላ ድርጅት (TCCC) ምንም እንኳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምርቶቹ ላይ ለውጥ ቢያመጣም፣ ሰባት ዝቅተኛ ካሎሪ/ኪሎጁዉል መጠን ያላቸው ለስላሳ መጠጦችን በማቅረብ ለደንበኞቹ አሁንም አማራጮችን በማቅረብ ላይ ይገኛል። 

ከሁለት ዓመት በፊት ኮካ ኮላ (TCCC) እንደ አለምአቀፍ ፖርትፎልዮ እደሳ አካል በመላው አለም በሚገኙ የተለያዩ ገበያዎች ውስጥ የተመረጡ ምርቶችን እንደሚያቋርጥ አስታውቋል።

"ይህ ምርት በአገሪትዋ ከሚቀርቡት ምርቶች ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ነው፤ ይህም የሚያመላክተው በ 2020 እ.ኤ.አ ድርጅቱ ያሳወቀው የምርት እደሳ ዜና የደንበኞችን እርካታ እና ፍላጎት ያስቀደመ እንደሆነ ነው።" በማለት የኮካ ኮላ ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር ሲልኬ በከር ተናግረዋል። 

እንደ በከር አገላለጽ፦ "ይህ እደሳ የደንበኛ ተኮር ምርህን በመከተል የኢንቨስትመንት ትኩረትን ከመለወጥ ጋር የተያያዘ እንጂ የኮካ ኮላን (TCCC) ምርቶች ከማቃለል ጋር አይያያዝም።" 

"በእደሳው የመጡት ዝቅተኛ ካሎሪ ወይም ኪሎጅዉል መጠን ምርቶች ለደንበኞቻችንን ቅድሚያ የመስጠት ዓላማ እንዳለን የሚያሳይ ነው።" በማለት ተናግራለች።

በእደሳው ምክንያት፣ ኮካ ኮላ (TCCC) TaB® በዓለም ደረጃ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ እንደሚያቋርጥ አሳውቋል። ይሁን እንጂ ከ1990ዎች እ.ኤ.አ በግምባር ቀደምነት ዝቅተኛ ካሎሪ መጠጥን እንደ አማራጭ ያቀረበው ድርጅት አሁንም ለደንበኞቹ አቻ ያልተገኘለት ዝቅተኛ ካሎሪ መጠጦችን በማቅረብ ላይ ይገኛል።

ከእነዚህ ውስጥ አራቱ አዳዲስ ምርቶች በኮካ ኮላ® ምርት ስም ይታሸጋሉ። እነዚህም በ 2021 እ.ኤ.አ የደቡብ አፍሪካ "ምርጥ ቀዝቃዛ መጠጥ" ተብሎ በሰንደይ ታይምስ ጂንኔክስት ዳሰሳ ጥናት (Sunday Times GenNext Survey) ተሰይሟል። 

እነዚህም ኮካ ኮላ® ከስኳር ነጻ፣ ኮካ ኮካ® ላይት፣ ኮካ ኮላ® ኦሪጅናል ጣዕም እና ኮካ ኮላ® ከስኳርና ከካፊን ነጻ ናቸው። ሌሎቹ ፋንታ® ከስኳር ነጻ፣ ስፕራይት® ከስኳር ነጻ እና ስቶኒ® ከስኳር ነጻ የዝንጅብል ቢራ ናቸው። 

"ለዝቅተኛ ካሎሪ ምርታችን መንገድ ስላመቻቸልን TaB ን እናም ለ6 አስርት ዓመታት ተቀብለው ላቆዩት የTaB አፍቃሪያንን ማመስገን እንወዳለን። በዚህ ዘርፍ ውስጥ ኮካ ኮላ ከስኳር እና ከካፊን ነጻ ይካተታል። የ TaB ምትክ እንደሆነ በሰፊው የሚታወቀው ተመሳሳይ የሆነ ጥቅም ያለምንም የጣዕም እና ጥራት ለውጥ አገልግሎት ይሰጣል።" በማለት በከር ደምድማለች።

ዓለም አቀፍ የምርት እደሳ ኮካ ኮላን (TCCC) የተሻለ እንዲሰራ እና ምርቶቹን በተለየ መንገድ እንዲመለከተው አድርጎታል፤ ይህም ሙሉ በሙሉ የመጠጥ ድርጅት የመሆን እቅዱን እንዲያሳካ ያግዘዋል። እንደ ከስኳር እና ከካፊን ነጻ የመሳሰሉ የኮካ ኮላ አዳዲስ ምርቶች ድርጅቱን ለደንበኞቹ ስለ ምርጫዎቻቸው እንዲያውቁ እና በራስ የመመራት እና በፍጆታ ምርጫቸው ላይ ልዩነት እንዲኖራቸው ለማድረግ የኩባንያዉን ታማኝነት የሚያሳይ ነው።

ጠቀሚ ሆኖ ለመገኘት ሲል TCCC የደንበኞቹን ሀሳብ በማዳመጥ እና ተገቢውን መልስ በመስጠት የሚፈልጉትን መጠጥ ማቅረብ ይፈልጋል።