የኮካ ኮላ የአገልግሎት ውሎች
ተፈጻሚ የሚሆንበት ቀን፦ 16/02/2023
ወደ ኮካ ኮላ የአገልግሎት ውሎች ("ውሎች") እንኳን በደህና መጡ
እባክዎን በደንብ ያንብቡት ምክንያቱም እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች በእርስዎ እና በኮካ ኮላ ድርጅት እና ሸሪኮቹ (በአንድ ላይ ኮካ ኮላ ወይም እኛ) መካከል የሚገባ ህጋዊ ስምምነት ነው።
እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች ከኮካ ኮላ ጋር የሚኖሮትን ግጭት የሚፈቱበት አካሄድ ላይ ተጽኖ ያሳድራሉ።
1. መግቢያ
እነዚህ ውሎች የኮካ ኮላን ድረ ገጾች፣ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያዎች፣ ዊጄቶች እና ሌሎች የኦንላይን እና ኦፍላይን አገልግሎቶችን ለማግኘት እና ለመጠቀም የሚያገለግሉ ውሎች እና መመሪያዎችን ያስቀምጣሉ። የዚህ አገልግሎት ሰጪ ኮካ ኮላ ድርጅት፣ One Coca‑Cola Plaza, Atlanta, Georgia 30313 ነው።
እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች የተመዘገቡ ተጠቃሚ ወይም ተራ ተጠቃሚ ከሆኑ ይመለከቶታል።
አገልግሎቶችን በሚጠቀሙ እና በሚያገኙ ጊዜ እነዚህን ውሎች ማክበር እና መቀበል አለብዎት። ከእነዚህ ውሎች ጋር የማይስማሙ ከሆነ፣ እባክዎን አገልግሎቶችን አይጠቀሙ።
ከተጠቃሚዎች ወይም ስለተጠቃሚዎች ኮካ ኮላ ስለሚሰበስበው መረጃ ማወቅ ከፈለጉ እባክዎን የኮካ ኮላ የደንበኞች የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲን (ወይም ለእርስዎ ቅርብ የሆነ ፖሊሲ ወይም ማሳሰቢያን) ይመልከቱ።
2. እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች ተግባራዊ የሚሆኑት መቼ ነው?
እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች ለአዲስ ተጠቃሚዎች ከላይ በተጠቀሰው የተፈጻሚነት ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናሉ። ከላይ ከተጠቀሰው ቀን በፊት አገልግሎቶቻችንን የሚጠቀም ሰው፣ ከዚህ ቀደም የነበሩት ውሎች ተፈጻሚ ከሚሆንበት ቀን ጀምሮ በኋላ ላሉት አስር (10) ቀናት ይሰራሉ።
መለያ በሚከፍቱበት ጊዜ፣ አገልግሎቶቻችንን በሚጠቀሙ ጊዜ ወይም ለመጠቀም በሚስማሙ ጊዜ፣ አገልግሎቶቹን ለመጠቀም ብቁ መሆንዎን እንዲሁም ለውሎቹ ተገዢ እንደሚሆኑ ለኮካ ኮላ እያሳወቁ ነው።
አገልግሎቶቻችንን ለመጠቀም፣ ነዋሪ የሆኑበት አገር ህግ የሚፈቅደው እድሜ መሆኑን ወይም ከኮ ኮላ ጋር ህጋዊ ስምምነት ውስጥ መግባት እንደሚችሉ ያረጋግጡ።
ነዋሪ በሆኑበት አገር ህግ መሰረት አገልግሎት ለማግኘት እድሜዎ ካልደረሰ ወይም ከኮካ ኮላ ጋር ህጋዊ ስምምነት ውስጥ መግባት ካልቻሉ፣ አገልግሎቶቹን ከመጠቀምዎ በፊት ለእነዚህ ውሎች ወላጅዎ ወይም አሳዳጊዎ መስማማት ይኖርበታል። አገልግሎቶችን ከመጠቀምዎ በፊት ወላጅዎን ወይም አሳዳጊዎን ስለእነዚህ ውሎች እንዲነግርዎ ይጠይቁ።
ወላጆች እና ህጋዊ አሳዳጊዎች፦ ህጻን ልጅ ወክለው እነዚህን ውሎች የሚቀበሉ ከሆነ፣ ለኮካ ኮላ ወላጅ ወይም ህጋዊ አሳዳጊ መሆንዎን እየተስማሙ ነው፤ እነዚህን ውሎች ተቀብለው የኮካ ኮላን የደንበኞች የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ (ወይም ሌሎች ለእርስዎ ቅርብ የሆኑ የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲዎች ወይም ማሳሰቢያዎች) ላይ ልጅዎን ወክለው ፍቃደኝነትዎን እየሰጡ ነው፤ እናም በእነዚህ ውሎች መሰረት የልጅዎን የአገልግሎቶቻችን አጠቃቀም በተመለከተ ኃላፊነት እየወሰዱ ነው።
አገልግሎቶቻችንን ለመጠቀም ብቁ ካልሆኑ ወይም በእነዚህ ውሎች ካልተስማሙ አገልግሎቶቻችንን መጠቀም አይችሉም።
3. እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች ተግባራዊ የሚሆኑት የት ነው?
እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች ተግባራዊ የሚሆኑት የተያያዙበት ቦታ ወይም የተለጠፉበት ቦታ ላይ ነው።
ለሰራተኞች፣ ስራ አመልካቾች፣ እና የኮካ ኮላ የቢዝነስ ደንበኞች እና አጋሮች እና ለተወሰኑ የኮካ ኮላ ኮርፖሬት ድረ ገጾችን የኦንላይን አገልግሎቶችን በሚጠቀሙ ጊዜ የተለያዩ ውሎች እና መመሪያዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ከአገልግሎቶቻችን ጋር ለተያያዙ ሶስተኛ ወገን አገልግሎት ሰጪዎችም (ለምሳሌ፦ Whats App) የተለያዩ ውሎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ክፍል 12ን ከታች ይመልከቱ።
ለአገልግሎቶቻችን የተወሰኑ ክፍሎች ማለትም ለመተግበሪያዎች፣ ለማስታወቂያዎች፣ ለሽያጭ ውሎች ወይም የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶች ተጨማሪ ውሎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ሁሉም ተጨማሪ ውሎች የእነዚህ ውሎች አካል (እና በዚህ አንቀጽ ተካታች) ናቸው። እነዚህ ውሎች ለእርስዎ በሚቀርቡበት ጊዜ፣ አገልግሎቶቻችንን ከመጠቀምዎ በፊት እነዚህን ተጨማሪ ውሎች መቀበልዎን መስማማት አለብዎት። የተጨማሪ ውሎች እና መመሪያዎች አንቀጾች ከዚህ ውሎች እና መመሪያዎች ጋር የሚጻረሩ ካልሆነ በቀር (በዚህ ጊዜ ተጨማሪ ውሎች እና መመሪያዎች ስህተቶችን ሳያካትቱ የበላይ ይሆናሉ) እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች እና ተጨማሪ ውሎች እና መመሪያዎች በእኩል ተፈጻሚ ይሆናሉ።
የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶች
አንድ አንድ አገልግሎቶች የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎት (SMS ወይም MMS) ይሰጣሉ። የጽሁፍ መልዕክት ከእኛ ለመቀበል ሲስማሙ፣ የምንልክሎት የጽሁፍ መልዕክት መጠን ከእኛ ጋር በሚኖርዎ የገንዘብ ዝውውሮች ብዛት ይወሰናል። ከአገልግሎቶች ጋር ወደተገናኘው ልዩ የሞባይል ኮድ "አቁም" የሚል የጽሁፍ መልዕክት በመላክ የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶችን ማስቆም ይችላሉ። የጽሁፍ መልዕክት እና የውሂብ ክፍያዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። የገመድ አልባ ኔትወርክ አገልግሎት ሰጪዎ ሁሉንም ክፍያዎች ይቀበላል። የክፍያውን እቅድና ዝርዝር ማወቅ ከፈለጉ እባክዎ የገመድ አልባ ኔትወርክ አገልግሎት ሰጪዎን ያነጋግሩ። የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎቶች የሚሰጡት "ባለበት ሁኔታ" እንጂ በሁሉም ቦታዎች እና በሁሉም ጊዜ ላይኖሩ ይችላሉ።
የጽሁፍ መልዕክቶች ለመቀበል ሲስማሙ፣ ኮካ ኮላን አውቶማቲክ መደወያ ሲስትሙን ተጠቅሞ የጽሁፍ መልዕክት እንዲልክልዎ እየተስማሙ ነው። በተጨማሪም የጽሁፍ መልዕክት ለመቀበል ያሳዩት ፈቃደኝነት ከምርትና አገልግሎቶች ሽያጭ ጋር እንደማይገናኝ በመስማማት ነው።
4. ኮካ ኮላ አገልግሎቶቹን ይቀይራል?
ኮካ ኮላ አገልግሎቶቹን ለማሻሻል ሁልጊዜ ይሰራል። ኮካ ኮላ አገልግሎቱን የሚያሻሽሉለትን እና ከዚህ በፊት የአገልግሎቶቹ ("አዳዲስ ነገሮች") አካል ያልነበሩ "አዳዲስ ነገሮች" እና ተግባራትን ሊያስተዋውቅ ይችላል። የተጠቃሚውን ምቾት ከፍ ለማድረግ ኮካ ኮላ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአገልግሎቶች ዝማኔዎችን፣ እርማቶችን ወይም ሌሎች ለውጦችን ("ዝማኔዎች") ሊያካሂድ ይችላል። ኮካ ኮላ አዳዲስ ነገሮችን የመጨመርም ሆነ ያለመጨመር ወይም ዝማኔዎችን የማድረግም ሆነ ያለማድረግ መብት አለው። አዲሶቹ ዝማኔዎች ክፍያ የሚጠይቁ ከሆነ፣ ኮካ ኮላ አዳዲስ ነገሮችን የመጠቀም አማራጭ ያቀርብሎታል። ኮካ ኮላ ዝማኔዎችን ካደረገ ለእርስዎ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ወይም ማስጠንቀቂያ ሰጥቶዎት እነዚህን ዝማኔዎች ኮካ ኮላ ተግባራዊ እንዲያደርግ ይስማማሉ እንዲሁም ፍቃድ ይሰጣሉ።
ለብዙሀን ከመቅረቡ በፊት ኮካ ኮላ አዳዲስ ነገሮችን እርስዎ ብቻ እንዲሞክሩት ለእርስዎ ብቻ ተገኚ ሊያደርግ ይችላል። ሌሎች ከማግኘታቸው በፊት እርስዎ እንዲሞክሩ የሚቀርቡ አዳዲስ ነገሮችን "የሙከራ አገልግሎቶች" ብለን እንጠራቸዋለን። የሙከራ አገልግሎቶችን የማግኘት መብትዎን ከግምት ውስጥ በማስገባት በኮካ ኮላ ምክንያታዊ በሆነ ጥያቄ መሰረት ለዚህ አገልግሎት አስተያየትዎን ለመስጠት ይስማማሉ። ኮካ ኮላ ያለምንም ማስጠንቀቂያ የሙከራ አገልግሎቶች የዋናው አገልግሎት አካል ከመሆናቸው በፊት የማስተካከል መብት አለው። የሙከራ አገልግሎቶቹን የዋናው አገልግሎት አካል ያለማድረግ መብትም ጭምር አለው።
የእነዚህ ውሎች አካል የሆኑትን ስለእኛ ኃላፊነት የሚያነሱ ሌሎች ክፍሎችን በማይጻረር መልኩ፣ የሙከራ አገልግሎቶች ያለምንም ዋስትና "ባሉበት ሁኔታ" የሚሰጡ ይሆናል። የኮካ ኮላ አካላት (በክፍል 13 እንደተተረጎመው) የእርስዎን የሙከራ አገልግሎቶች አጠቃቀም በተመለከተ ምንም ኃላፊነት የለባቸውም። የሙከራ አገልግሎቶቹን በተመለከተ ከኃላፊነት የሚያርቅ ህግ ተፈጻሚ መሆን ካልቻለ፤ የሙከራ አገልግሎቶቹን በተመለከተ የኮካ ኮላ አካላት ብቸኛ ኃላፊነት የሚሆነው የሙከራ አገልግሎቱን በሚጠቀሙ ጊዜ የከፈሉት ክፍያ የእርስዎ ቀጥተኛ ኪሳራ ይሆናል።
በዚህ ክፍል 4 ውስጥ የተጠቀሱት ኮካ ኮላ አገልግሎቱን በተወሰነ መልኩ ከመገደብ ወይም አገልግሎቱን ከማቋረጥ ወይም የትኛውም የምናቀርበውን ይዘት በየትኛውም ሰዓት ያለምንም ማስጠንቀቂያ ወይም ለእርስዎ ኃላፊነት ሳይኖርበት ከማቋረጥ አይከለክለውም። አገልግሎቶቻችን ሁልጊዜ ሙሉ በሙሉ ያለማቋረጥ እየሰሩ እንደሆነ ለማረጋገጥ የአቅማችንን ያህል እንሰራለን። ነገር ግን አገልግሎቶቹ በየትኛውም ምክንያት ቢቋረጥ ኮካ ኮላ በእርስዎ ተጠያቂ አይሆንም።
5. ኮካ ኮላ እነዚህን ውሎች እና መመሪያዎች ሊቀይር ይችላል?
እነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች ተፈጻሚ የመሆኑበት ቀን ከዚህ ድረ ገጽ ራስጌ ላይ ተጠቅሷል።
ኮካ ኮላ ዝማኔዎች ሲኖሩ፣ አዳዲስ ነገሮች ሲጨመሩ እንዲሁም ህጎች ሲሻሻሉ እነዚህን ውሎች እና መመሪያዎች ሊያሻሽል ይችላል። ኮካ ኮላ ህጋዊ መብቶችን የሚቀንሱ ማስተካከያዎችን በእነዚህ ውሎች ላይ ቢያካሂድ፣ ከሰላሳ (30) ቀናት ቀደም ብሎ በአገልግሎቶች ገጽ ላይ ይለጥፋል ወይም ተጠቃሚዎች መለያዎቻቸውን በከፈቱበት የኢሜይል አድራሻ ያሳውቃል። የውሎቹን ማሻሻያ ካልተቀበሉት የማሳሰቢያው ቀን ከማለፉ በፊት መለያዎን በመዝጋት አገልግሎቶቻችንን መጠቀም ማቆም ይኖርቦታል። አገልግሎቶቻችንን ከማሳሰቢያው ቀን በኋላም መጠቀም ከቀጠሉ የውሎች ማሻሻያውን እንደተቀበሉ ማረጋገጫ ይሆናል።
ህግ እንድናሻሽል እስካላስገደደን ድረስ ወይም የሌሎች ተጠቃሚዎችን መብት ለመጠበቅ ሲባል ካልሆነ በቀር ማሳሰቢያ ሳንልክ የእርስዎን ህጋዊ መብት የሚቀንስ ማሻሻያ አናደርግም።
የተሻሻለው ውሎች ቅድሚያ ከነበሩት የእነዚህ ውሎች ስምምነቶች፣ ማሳሰቢያዎች ወይም መግለጫዎች በላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
6. መለያ የግዴታ ያስፈልጋል?
ለህዝብ የቀረቡትን የኮካ ኮላ ድረ ገጾች ለመጎብኘት መለያ መክፈት አይጠበቅቦትም። ነገር ግን የአገልግሎቶቻችንን ሙሉ ጥቅም ለማግኘት ማለትም ሽልማቶችን ለማግኘት ወይም ሌሎች ማስታወቂያዎችን ወይም "ለአባላት ብቻ" የሚለውን የአገልግሎቶቻችን ክፍል ለመጠቀም መለያ መክፈት ሊኖርቦት ይችላል።
መለያ ለመክፈት ቢያንስ ኢሜይልዎን ማሳወቅ አለብዎት። አገልግሎቶችን ለማግኘት የትውልድ ቀን እና የመኖሪያ አድራሻዎን እንዲያሳውቁ ኮካ ኮላ ሊያስገድድ ይችላል። ይህም ኮካ ኮላ ጋር ስምምነት ማድረግ የሚችል ህጋዊ አካል እንደሆኑ ለማረጋገጥ ወይም ወላጅዎ ወይም አሳዳጊዎ እርስዎን ወክለው ለእነዚህ ውሎች ስምምነት እንዲፈጽሙ ለማድረግ ነው።
መለያዎን በሚከፍቱ ጊዜ በፈቃደኝነት ኮካ ኮላ ስምዎን፣ ስልክ ቁጥርዎን፣ ፍላጎትዎን፣ ሀሳብዎን ወይም ሊያጋሩን የሚወዱት ስለ እርስዎ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን የመሳሰሉ ተጨማሪ መረጃዎችን ኮካ ኮላ ሊጠይቅዎ ይችላል። መለያ ሲከፍቱ ከእርስዎ የምንሰበስበውን የግል መረጃ እንዴት እንደምንጠቀመው ለማወቅ ከፈለጉ፣ እባክዎን የኮካ ኮላ የደንበኞች የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ (ወይም መለያ ሲከፍቱ የተስማሙበትን ሌላ የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ወይም ማሳሰቢያ) ይመልከቱ።
በኮካ ኮላ በኃላፊነት የተመሰረተው ማርኬቲንግ ፖሊሲ ላይ እንደተጠቀሰው ከ 13 ዓመት (ወይም በእርስዎ አገር በህግ ከተፈቀደው ዝቅተኛ እድሜ) በታች ለሆኑ ህጻናት ማስታወቂያ አናዘጋጅም። በመሆኑም፣ አገልግሎቶቻችን ከ 13 ዓመት (ወይም በእርስዎ አገር በህግ ከተፈቀደው ዝቅተኛ እድሜ) በታች ለሆኑ ህጻናት አልተዘጋጀም ወይም አልታሰበም።
ከእርስዎ ውጭ ለሌላ ሰው መለያ እንደማይከፍቱ፣ ሌላ ሰው በማስመሰል መለያ እንደማይከፍቱ፣ ወይም የኮካ ኮላን የብቁነት ማጣሪያ ስርዓት እንደማያታልሉ ይስማማሉ። የእነዚህን ውሎች ጥሰት ካስተዋለ ወይም ከጠረጠረ፣ ኮካ ኮላ የመለያ ምዝገባን የመከልከል ወይም የመሰረዝ ወይም የማገድ መብት አለው። አገልግሎቶቻችንን ከመጠቀም ከዚህ ቀደም ታግደው ወይም ተሰርዘው ከሆነ መለያ መክፈት አይችሉም።
ለኮካ ኮላ የሚሰጡት መረጃ እውነተኛ፣ ትክክለኛ እና የተሟላ እንደሆነ እና ሁሌም እንደዚሁ እንደሚቀጥል ቃል ይገባሉ።
መለያ በሚከፍቱ ጊዜ የይለፍ ቃል ከተጠየቁ የይለፍ ቃልዎ የግልዎ ብቻ ነው። ወደ አገልግሎቶቻችንን የሚያስገባ የደህንነት መረጃን ወይም የይለፍ ቃልዎን ሌላ ሰው አሳልፈው እንደማይሰጡ ይስማማሉ። በህዝብ መጠቀሚያ ወይም በጋራ ኮምፒውተር ወይም ስልክ በሚጠቀሙበት ጊዜ ሰዎች የይለፍ ቃልዎን ወይም ሌላ የግል መረጃዎን እንዳይመለከቱ እባክዎ ወደ መለያዎ ሲገቡ ልዩ ጥንቃቄ ያድርጉ። የይለፍ ቃልዎ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ማንኛውም እንቅስቃሴ ኃላፊነቱ የእርስዎ ነው።
የይለፍ ቃልዎ፣ መለያዎ ላይ ፍቃድ የሌለው እንቅስቃሴ ወይም ጥቅም ላይ መዋልን ካስተዋሉ ወይም ከጠረጠሩ ወዲያውኑ በሚከተለው አድራሻ https://www.coca-colacompany.com/contact-us እንደሚያሳውቁን ይስማማሉ።
7. ኮካ ኮላ ለአገልግሎቶቹ ክፍያ ይጠይቃል?
በአጠቃላይ አገልግሎቶቻችን ነጻ ነው። ለአገልግሎቶች አንድ አንድ ልዩ ባህሪያት ክፍያ ከተጠየቁ፣ ኮካ ኮላ የመክፍል ወይም ያለመክፈል አማራጮችን ያቀርብሎታል።
አንድ አንድ አገልግሎቶች የኮካ ኮላን ምርቶች እንዲገዙ ሊፈቅዱ ይችላሉ። ግዢዎች የራሳቸው የሆነ በግዢ ሰዓት የሚቀርቡ የሽያጭ ውሎች እና መመሪያዎች አሏቸው – እባክዎን በደንብ ያንብቧቸው።
አገልግሎቶቻችን በሚጠቀሙ ጊዜ ለሚኖሩ ክፍያዎች እና ሌሎች ወጪዎች ኃላፊነቱ የእርስዎ ብቻ ነው። አገልግሎቶቻችንን ለማግኘት መሰረታዊ የሆኑ ቴክኖሎጂ የመሳሪያ፣ የኢንተርኔት ወይም የስልክ ኔትወርክ አገልግሎቶችን ይጨምራል። በተንቀሳቃሽ ስልክዎ አገልግሎቶቻችንን ከተጠቀሙ ከኔትወርክ አግልግሎት ሰጪዎ አካል የሚቆረጥ ማንኛውም ክፍያ የእርስዎ ኃላፊነት ነው።
8. የአገልግሎቶቻችንን ባለቤት ማነው?
በእርስዎ እና ኮካ ኮላ መካከል እንዳለው፣ ኮካ ኮላ እና ሶስተኛ ወገን ፍቃድ ሰጪዎች በአገልግሎቶቻችን ውስጥ የሚገኙ ሁሉንም ይዘቶች፣ ዲዛይኖች፣ ምርጫና አቀማመጦች እና የአዕምሮ ንብረት መብቶችን ጨምሮ የአገልግሎቶቻችንን ስምና ፍላጎቶች (የአገልግሎት ይዘት) ብቸኛና ባለሙሉ መብት ባለቤቶች ናቸው ወደፊትም ይሆናሉ። ኮካ ኮላ የአገልግሎቶች ባለቤት ሲሆን ለይዘቶቹም ፍቃድ አለው። ከታች እንደተጠቀሰው እርስዎም የሚፈጥሩት የተጠቃሚ ይዘት ባለቤት ኖት።
የአገልግሎቶች ይዘት የኮካ ኮላ ስም፣ ተያያዥ ስሞች፣ ዓርማዎች፣ ምርቶች እና አገልግሎቶች ስም፣ ዲዛይን እና መፈክር (ኮካ ኮላ ምልክቶች)ያካትታል። ያለ የኮካ ኮላ በቅድሚያ የሚሰጥ የጽሁፍ ፍቃድ የኮካ ኮላን ምልክቶች መጠቀም የለብዎትም። በአገልግሎቶቻችንን ላይ የተጠቀሱ ሌሎች የኮካ ኮላ ወይም የሶስተኛ ወገን ስሞች፣ ዓርማዎች፣ ምርቶችና የአገልግሎት ስሞች፣ ዲዛይኖች፣ መፈክሮች፣ ጥቅሶች ወይም አርዕስቶች ባለቤትነቱ ለሚመለከተው አካል ይሆናል።
በእነዚህ ውሎች ውስጥ ከተጠቀሰው ውጪ የአገልግሎቶች ይዘትን በተመለከተ መብት፣ ፍቃድ ወይም ባለቤትነት መብት የሎትም። አገልግሎቶቻችንን በዓለም አቀፍ የቅጂ መብት፣ የንግድ ምልክት፣ የባለቤትነት መብት፣ የንግድ ሚስጥር እና በሌሎች የአዕምሮ መብት ወይም በፕሮፕራይተሪ መብት ህግጋት የተጠበቀ ነው። ግልጽ ለማድረግ፤ እርስዎ የሚከተሉትን ለማድረግ (ወይም ማንኛውም ሶስተኛ ወገንም የሚከተሉትን እንዲያደርግ) ይስማማሉ፦
- በአገልግሎቶቻችንን ውስጥ የተጠቀሱ የንግድ መብት፣ የንግድ ምልክት ወይም ሌሎች የፕሮፕራይተሪ መብቶች ማሳሰቢያዎችን እንደማያስወግዱ።
- የኮካ ኮላን የጽሁፍ ፍቃድ በቅድሚያ ሳያገኙ የአገልግሎቶችን ልዩ ባህርያት የያዙ የራስዎን መረጃ ቋት እንደማይፈጥሩ እና/ወይም እንደማያትሙ።
- በእነዚህ ውሎች በግልጽ ከተቀመጠው ውጪ ማንኛውንም ዓይነት የአገልግሎቶች ይዘት እንደማያባዙ፣ እንደማያከፋፈሉ፣ እንደማያሻሽሉ፣ ተመሳሳይ ይዘቶችን እንደማያፈጥሩ፣ ለህዝብ እይታ እንደማያቀርቡና እንደማያሳዩ፣ መልሰው እንደማያትሙ፣ እንደማያወርዱ፣ እንደማያስቀምጡ ወይም እንደማያሰራጩ።
- ከአገልግሎቶቻችን የትኛውም ክፍል መረጃ ለመሰብሰብ ሮቦት፣ ስፓይደር፣ የመፈለጊያ መተግበሪያዎች ወይም ተመሳሳይ አውቶማቲክ መሳሪያዎችን መጠቀም፣ መረጃን ማቀናበሪያ ወይም ማግኛ መሳሪያዎችን መጠቀም።
- አገልግሎቶቻችንን በማንኛውም ሰዓት ሲጠቀሙ የኮካ ኮላን ወይም ሶስተኛ ወገን ባለፍቃዶችን የፕሮፕራይተሪ መብት እንደማይጥሱ ወይም እንደማይጋፉ።
የራስዎ የተጠቃሚ ይዘት ባለቤት ኖት ግን ለኮካ ኮላ የመጠቀሚያ መብት ሰጥተዋል።
አገልግሎቶቻችን እርስዎ እና ሌሎች ተጠቃሚዎች መለጠፍ፣ ማስገባት፣ ማተም፣ ማሳየት ወይም ይዘትን ወይም መርጃዎችን (በአጠቃላይ፤ የተጠቃሚ ይዘት) ማሰራጨት የሚችሉበት ፎረም ወይም ሌሎች መስተጋብራዊ ባህሪያት ሊኖራቸው ይችላል። እርስዎ ያስገቡት የተጠቃሚ ይዘት ውሎች እና መመሪያዎች እስካልከለከሉ ድረስ ለሚፈጥሩት የተጠቃሚ ይዘት ባለቤትነቱ የእርስዎ ነው።
ለተጠቃሚዎች ይዘት ህጋዊነት፣ አስተማማኝነት፣ ትክክለኝነት እና አግባብነት ኃላፊነት እንዳለብዎ ይረዳሉ እናም ይስማማሉ።
የተጠቃሚ ይዘት በአገልግሎቶቻችን ወይም በኮካ ኮላ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ቢያስገቡም፣ ለኮካ ኮላ (በአገልግሎቶቻችችን ስራ ላይ ለሚያግዙን አቅራቢዎች እና ሌሎች ተተኪዎችና ወኪሎች) ያልተገደበ፣ ዘላቂ፣ ዓለም አቀፍ፣ በብቸኝነት ያልሆነ፣ ያለክፍያ፣ ሙሉ በሙሉ ከክፍያ ነጻ የሆነ ፍቃድ ይሰጣሉ። በተጨማሪም እንዲጠቀም፣ እንዲያቆይ፣ እንዲያቀርብ፣ እንዲያባዛ፣ እንዲያስተካክል፣ ለህዝብ እያታ እንዲያቀርብ፣ እንዲተረጉም፣ እንዲያከፋፍል እና ለሶስተኛ ወገን የእርስዎን የተጠቃሚ ይዘት እንዲያካፍል (በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ) ለማንኛውም ምክንያት፣ አሁን ባሉትም ወደፊትም በሚኖሩት በፈለገው ሚዲያ በህግ እስከተፈቀደ ድረስ ፍቃድ ለኮካ ኮላ ይሰጣሉ። በእነዚህ ውሎች እና መመሪያዎች ውስጥ ለኮካ ኮላ የሚሰጡት ፈቃድ የትኛውም የሞራል መብቶች ወደ ተጠቃሚው ይዘት ፍቃድ አይተላለፍም። ለኮካ ኮላ የተጠቃሚ ይዘት ፍቃድ መስጠት ካልፈለጉ እባክዎን የተጠቃሚ ይዘት አያስገቡ።
የተጠቃሚ ይዘት በሚያስገቡበት ጊዜ፣ የሚከተሉትን መግለጫ እና ዋስትና ለኮካ ኮላ ይሰጣሉ፦
- በእነዚህ ውሎች መሰረት የተጠቃሚ ይዘትዎ የእርስዎና በእርስዎ ቁጥጥር ስር ያለ እንደሆነ እና ለኮካ ኮላ መብት እና ፍቃዱን አሳልፈው መስጠት እንደሚችሉ ይገልጻሉ።
- የተጠቃሚ ይዘትዎ የሌሎች ሰዎችን ወይም ተቋማትን መብት ይህም የግላዊነት መብትን፣ የማስታወቂያ እና የአእምሮ ንብረት መብትን አይጥስም።
- የተጠቃሚ መረጃዎ እውነተኛ እና ትክክለኛ ነው።
- የተጠቃሚ ይዘትዎ እነዚህን ውሎች እና መመሪያዎች፣ ሌሎች ህጎችን፣ ትዕዛዛትን እና ደንቦችን ያከብራል።
የተጠቃሚ ይዘትዎ ከሚከተሉት ህጎች ጋር መጣጣም አለባቸው፦
- የተጠቃሚ ይዘት ማንኛውንም ስም የሚያጠፋ፣ ጸያፍ፣ ጨዋነት የጎደለው፣ ተሳዳቢ፣ ስርዓት አልበኛ፣ ተንኳሽ፣ ዐመፀኛ፣ ደም ያለበት፣ የጥላቻ፣ ነገር ቆስቋሽ ወይም በሌላ መልኩ የተጠሉ ነገሮችን መያዝ የለበትም።
- የተጠቃሚ ይዘት በዘር፣ በሃይማኖት፣ በዜግነት፣ በአካል ጉዳት፣ በፆታ፣ በፆታዊ ዝንባሌ፣ በፆታ ማንነት ወይም በእድሜ ላይ የተመሰረተ ግልጽ ወሲባዊ ወይም የወሲብ ስራ፣ ጥቃትን ወይም መድልዎን ማስተዋወቅ የለበትም።
- የተጠቃሚው ይዘት ማንንም ሰው የሚያታለል ወይም የማታለል ዝንባሌ ያለው መሆን የለበትም።
- የተጠቃሚው ይዘት ማንኛውንም ህገወጥ ተግባር ማበረታታት፣ ወይም ማስተዋወቅ ወይም ማንኛውንም ህገወጥ ድርጊት ማገዝ የለበትም።
- የተጠቃሚው ይዘት ማንነትዎን ወይም ከማንም ሰው ወይም ድርጅት ጋር ግንኙነት ያልዎት በማስመሰል አሳሳች መሆን የለበትም ወይም የተጠቃሚ ይዘትዎ በኮካ ኮላ ወይም በሌላ ሰው ወይም አካል የተረጋገጠ ነው የሚል አስተያየት መስጠት የለበትም።
የተጠቃሚው ይዘት እነዚህን ውሎች እና መመሪያዎች ይጥሳል ብለው ካመኑ፣ እባክዎን በ https://www.coca-colacompany.com/contact-us ላይ ያሳውቁን። የትኛው የተጠቃሚ ይዘት እንደሆነ እና በአገልግሎቶቻችን ውስጥ ወይም በኮካ ኮላ ማህበራዊ ሚዲ ገጽ ላይ የቱ ጋር እንደሚገኝ ያሳውቁን። ህግ በሚፈቅደው መጠን ከተጠቃሚ ይዘትዎ ጋር በተያያዘ ከሶስተኛ ወገን ለሚነሱ ሁሉም የይገባኛል ጥያቄዎች ኮካ ኮላን ተጠያቂ ላለማድረግ ተስማምተዋል።
ከተጠቃሚ ይዘት በተጨማሪ፣ ኮካ ኮላን ስለ አገልግሎቶቹ (ግብረመልስ) ሃሳቦችን፣ ጥቆማዎችን ወይም ሌሎች ግብረመልሶችን ለመስጠት ከጊዜ ወደ ጊዜ መወሰን ይችላሉ። ሀሳብ ለመስጠት፣ እባክዎን ድረ ገጻችንን ላይ https://www.coca-colacompany.com/contact-us/submit-an-idea የሚለውን ይጎብኙ እና እዚያ ያለውን መረጃ ይመልከቱ። የግብረመልስዎ ባለቤት ኖት ነገር ግን ለኮካ ኮላ ግብረ መልስዎን በመስጠትዎ፣ ሁሉንም ግብረ መልስዎን ሙሉ በሙሉ የሚከፈል፣ ከሮያሊቲ-ነጻ፣ ዘላቂ፣ የማይሻር፣ ዓለም አቀፍ፣ በብቸኝነት ያልሆነ እና ሙሉ በሙሉ ፍቃድ ያለው መብት እና የመጠቀም፣ የማባዛት፣ የማከናወን፣ የማሳየት፣ የማሰራጨት፣ የማሻሻል፣ የማስተካከል እንደገና የመቅረጽ እና ተመሳሳይ ስራዎችን የመፍጠር፣ የመነሻ ስራዎችን መፍጠር እና በማንኛውም መንገድ የመጠቀም ፈቃድ ለኮካ ኮላ ሰጥተዋል እንዲሁም ተስማምተዋል። ያለ እርስዎ በቅድሚያ የሚሰጥ የጽሁፍ ፍቃድ በቀጥታ እስካልተለዩ ድረስ ኮካ ኮላ በአገልግሎቶቹ ውስጥ ግብረ መልስ ሊጠቀም እንደሚችል አምነዋል እንዲሁም ተስማምተዋል። ሁሉም የእርስዎ ግብረመልስ ምስጢራዊ እና ባለቤትነት የሌላቸው እንደሆኑ ይቆጠራሉ።
9. የተፈቀደላቸው የአገልግሎቶቹ አጠቃቀም ምንድን ናቸው?
በእነዚህ ውሎች ሲስማሙ ኮካ ኮላ ለንግድ ላልሆነ አገልግሎትዎ ብቻ የግል፣ የተገደበ፣ ብቸኛ ያልሆነ፣ የማይተላለፍ፣ የማይሻር እና አገልግሎቶቹን ማግኘት እና የመጠቀም እና መተግበሪያዎቹን አንድ (1) ቅጂ የማውረድ መብት ይሰጥዎታል።
አገልግሎቶቹን ለህጋዊ፣ ለግል እና ለንግድ ላልሆኑ ዓላማዎች ብቻ እንጂ ለማጭበርበር ዓላማ ወይም ከማንኛውም ህገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ መጠቀም የለብዎትም። ከላይ የተጠቀሱትን ሳይገድብ፤ ከታች የተጠቀሱትን ላለመሞከር፣ ላለማበረታታት ወይም ለማንም ሶስተኛ ወገን ላለመፍቀድ ይስማማሉ፦
- ያልተፈቀደ የአገልግሎቶቻችንን ወይም የኮካ ኮላን የኮምፒዩተር ሲስተሞች ወይም ኔትወርኮች በጠለፋ፣ ይለፍ ቃል በማጥመድ ወይም በሌላ መንገድ ማግኘት ወይም የማንኛውም ኮምፒውተር ወይም የደህንነት ደህንነትን በመጣስ ማግኘት (ወይም ለማግኘት መሞከር)።
- የኮካ ኮላን ሰርቨሮች ወይም ኔትወርኮች ሊጎዳ፣ ሊያሰናክል፣ ሊያጨናንቅ ወይም ሊያበላሽ እንደሚችል በሚያውቁት በማንኛውም መንገድ አገልግሎቶቹን መጠቀም።
- ማዳላት፣ መተንኮስ፣ ማስፈራራት፣ ማታለል፣ ማዋረድ፣ መጉዳት ወይም ማበሳጨት፣ ምቾትን መንሳት ወይም ጭንቀትን በሌሎች ላይ መፍጠር ወይም በሌላ በማንኛውም አካል የአገልግሎቶቹን አጠቃቀም እና ምቾት ላይ ጣልቃ መግባት (ወይም ጣልቃ ለመግባት መሞከር)።
- አገልግሎቶቹን ከራስዎ ሌላ በማንም ስም መጠቀም።
- ማንኛውንም የአገልግሎቶቹ ክፍል መቅዳት፣ ማሻሻል፣ ማሻሻል፣ መተርጎም፣ መልሶ መገንባት፣ መስበር ወይም በሌላ መንገድ ለመግባት መሞከር።
- በአገልግሎቶቻችን ውስጥ ያለውን ማንኛውንም የቅጂ መብት፣ የንግድ ምልክት ወይም ሌላ የባለቤትነት መብት ማስወገድ ወይም በሌላ መንገድ የማንኛውንም የሶስተኛ ወገን የአዕምሮአዊ ንብረት መብቶች መጋፋት ወይም መጣስ።
- ከአገልግሎቶቻችን የትኛውም ክፍል መረጃ ለመሰብሰብ ሮቦት፣ ስፓይደር፣ የመፈለጊያ መተግበሪያዎች ወይም ተመሳሳይ አውቶማቲክ መሳሪያዎችን መጠቀም፣ መረጃን ማቀናበሪያ ወይም ማግኛ መሳሪያዎችን መጠቀም።
- አገልግሎቶቹን ወይም የአገልግሎቱን ማንኛውንም ክፍል ወይም ተግባር ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን በማንኛውም ምክንያት መከራየት፣ ማከራየት፣ ማበደር፣ መሸጥ፣ የፍቃድ ፍቃድ መስጠት፣ መመደብ፣ ማከፋፈል፣ ማተም፣ ማዛወር ወይም በሌላ መልኩ እንዲገኝ ማድረግ።
- ምርቶችን እንደገና ለመሸጥ ወይም ለማከፋፈል በማቀድ የአገልግሎቶቹ አካል የሆኑትን ማንኛውንም የድረ ገጾች ክፍል እንደገና መቅረጽ ወይም ማሻሻል።
- ማንኛውንም ያልተፈቀደ ወይም ያልተፈለገ የንግድ ወይም የማስተዋወቂያ ይዘት በመላክ አገልግሎቶቹን መጠቀም።
ኮካ ኮላ የሚመለከተው ህግ በሚፈቀደው ልክ እና በኮካ ኮላ የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ መሰረት <ማስፈንጠሪያ> (ወይም ለእርስዎ የቀረበ ማንኛውም የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲ ወይም ማሳሰቢያ) በአገልግሎቶቹ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ የመቆጣጠር እና የመመዝገብ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮካ ኮላ እነዚህን ውሎች በመጣስ አገልግሎቶቹን እየተጠቀሙ ነው ብሎ ለማመን ምክንያታዊ መሰረት ካለው ኮካ ኮላ ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ አገልግሎቶቹን (ሌሎች ካሉት መፍትሄዎች በተጨማሪ) የማቋረጥ መብት አለው።
10. መተግበሪያዎቹን ለመጠቀም ማንኛውም ዓይነት ልዩ ውሎች አሉ?
በዚህ ክፍል 10 ላይ በግልጽ ከተገለጸው በስተቀር፣ እነዚህ ውሎች የእርስዎ የመተግበሪያ ማውረድ እና አጠቃቀም ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
ከድረ ገጽ በተለየ መልኩ፣ የሞባይል መተግበሪያ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልክዎ የሚወርድ እና የሚጫን ሶፍትዌር ነው። ምንም እንኳን ወደ ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ቢወርዱም መተግበሪያዎቹ ፈቃድ አላቸው - ለእርስዎም እየተሸጡ አይደሉም። በእነዚህ ውሎች መሰረት መተግበሪያዎቹን ከመጠቀም ውጪ በመተግበሪያዎቹ ላይ ምንም ዓይነት የባለቤትነት መብት ሊኖርዎ አይገባም።
የመተግበሪያውን ነጠላ ቅጂ ለግል፣ ለንግድ ላልሆነ አገልግሎት ብቻ በባለቤትነት ወይም በሌላ መንገድ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ማውረድ ይችላሉ። የተወሰኑ ተግባራትን ለእርስዎ ለማቅረብ የተወሰኑ የመተግበሪያ ክፍሎች የተንቀሳቃሽ ስልክዎን አገልግሎቶች እና ኢንተርኔት ማግኘት አለባቸው። የግል መረጃ በመተግበሪያዎቹ እንዴት እንደሚስተናገድ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የኮካ ኮላ የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲን <ማስፈንጠሪያ> (ወይም መተግበሪያ ሲያወርዱ ለእርስዎ የቀረበ ሌላ የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲን) ይመልከቱ።
መተግበሪያዎቹ እና የተቀሩት አገልግሎቶች አንድ ዓይነት ይዘት ላይኖራቸው ይችላል።
ዝማኔዎችን (በክፍል 4 ላይ እንደተገለጸው) ከጊዜ ወደ ጊዜ ለአንድ መተግበሪያ ልናቀርብ እንችላለን። በሞባይል ስልክዎ ቅንብሮች ላይ በመመስረት፣ ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከበይነመረቡ ጋር ሲገናኝ መተግበሪያው ያሉትን ሁሉንም ዝማኔዎች በራሱ መንገድ ያወርዳል እንዲሁም ይጭናል ወይም ያሉትን ዝማኔዎች ለማውረድ እና ለመጫን ጥያቄ ሊያቀርብሎት ይችላሉ። ሁሉንም ዝማኔዎች ለማውረድ እና ለመጫን ተስማምተዋል እና ካልተስማሙ መተግበሪያው በትክክል መስራት እንደማይችል አምነው ተስማምተዋል። በመተግበሪያ ላይ የሚደረጉ ሁሉም ዝማኔዎች የመተግበሪያው እና የአገልግሎቶቹ አካል ሆነው ይቆጠራሉ እንዲሁም ለእነዚህ ውሎች ተገዢ ናቸው።
ኮካ ኮላ ሁሉንም የኮካ ኮላ ምልክቶች (በክፍል 8 ላይ እንደተገለጸው) እና በኮካ ኮላ እና እርስዎ መካከል ያሉ ሌሎች የቅጂ መብቶች፣ የንግድ ምልክቶች እና ሌሎች አእምሯዊ መብቶችን ጨምሮ የመተግበሪያዎች ሙሉ መበት፣ ስያሜ እና ፍላጎት በእነዚህ ውሎች ውስጥ በግልጽ ከተሰጠዎት በስተቀር ይዟል።
ማናቸውንም መተግበሪያዎች ከአፕል App Store ወይም Google Play (እያንዳንዱ፣ የመተግበሪያ መድረክ) ሲያወርዱ ከታች ለተገለጹት እውቅና ይሰጣሉ እንዲሁም ይስማማሉ፦
- በኮካ ኮላ እና በመተግበሪያ መድረክ መካከል፣ ኮካ ኮላ ለመተግበሪያዎቹ ብቻ ተጠያቂ ነው።
- የመተግበሪያ መድረክ መተግበሪያውን በተመለከተ የጥገና እና የድጋፍ አገልግሎቶችን የመስጠት ግዴታ የለበትም።
- የእኛ መተግበሪያ ማንኛውንም የሚመለከተውን ዋስትና ማክበር ከተሳነው፦ (1) የመተግበሪያ መድረኩን ማሳወቅ ይችላሉ እናም የመተግበሪያ መድረኩ የአንድ መተግበሪያ የግዢ ዋጋን (የሚመለከተው ከሆነ) ተመላሽ ሊያደርግ ይችላል፣ (2) የሚመለከተው ህግ እስከ ሚፈቀደው መሰረት የመተግበሪያ መድረኩ ምንም አይነት የዋስትና ግዴታ አይኖረውም። እና (3) ሌሎች የይገባኛል ጥያቄዎች፣ ኪሳራዎች፣ ዕዳዎች፣ ጉዳቶች፣ ወጪዎች ወይም የዋስትና ደረጃን ማክበር ባለመቻል የሚከሰት ወጪ (በኮካ ኮላ እና በመተግበሪያ መድረክ መካከል እንደሆነው) የኮካ ኮላ ኃላፊነት ነው።
- የመተግበሪያ መድረኩ ከመተግበሪያዎቹ ወይም ከመተግበሪያዎቹ ይዞታ እና አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ያልዎትን ማንኛውንም የይገባኛል ጥያቄ የመመለስ ኃላፊነት የለበትም።
- አንድ ሶስተኛ ወገን አንድ መተግበሪያ የሌላ ወገን የአዕምሯዊ ንብረት መብቶችን ይጥሳል የሚል ከሆነ፣ (በመተግበሪያ መድረክ እና በኮካ ኮላ መካከል እንደሆነው) ኮካ ኮላ ለማንኛውም የአዕምሯዊ ንብረት ጥሰት የይገባኛል ጥያቄን የመመርመር፣ የመከላከል፣ የመፍታት እና የማስወገድ ኃላፊነት አለበት።
- መተግበሪያን የመጠቀም መብትን በተመለከተ እና ከሚመለከተው የአጠቃቀም ውሎች አንጻር የመተግበሪያ መድረኩ እና ተባባሪዎቹ የሶስተኛ ወገን ተጠቃሚዎች ናቸው። የአጠቃቀም ውሎች እና መመሪያዎችን ከተቀበሉ በኋላ፣ የመተግበሪያ መድረኩ (እንደ ሶስተኛ ወገን ተጠቃሚ) ከእርስዎ የመተግበሪያ ፈቃድ ጋር በተዛመደ የአጠቃቀም ውሎችን የማስከበር መብት ይኖረዋል (እና መብቱን እንደተቀበለ ይቆጠራል)።
- እንዲሁም መተግበሪያውን በሚጠቀሙበት ጊዜ ሁሉንም የሶስተኛ ወገን ውሎች በመተግበሪያ መድረኩ አማካኝነት ማክበር አለብዎት።
በማናቸውም መተግበሪያዎች ስለሚሰበሰበው የተለየ መረጃ የበለጠ ለማወቅ፣ እባክዎ የተንቀሳቃሽ ስልክዎን ቅንብር ይመልከቱ ወይም መተግበሪያውን ባወረዱበት የመተግበሪያ መድረክ ላይ ይፋዊ መግለጫዎችን ይገምግሙ። መተግበሪያው ምንም ዓይነት መረጃ እንዲሰበስብ ካልፈለጉ፣ መተግበሪያውን ያስወግዱት።
በሚከተሉት ላይ ይስማማሉ እንዲሁም ዋስትና ይሰጣሉ፦ (1) በአሜሪካ ግዛት ውስጥ የሚገኝ አካባቢ ውስጥ የመንግስት እገዳ ያለበት ሀገር ውስጥ ወይም በአሜሪካ መንግስት እንደ "አሸባሪ ደጋፊ" ሀገር የተሰየመ ሀገር ውስጥ አይገኙም፤ እና (2) በማንኛውም የአሜሪካ መንግስት የተከለከሉ ወይም የታገዱ አካላት ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም።
11. እነዚህ ውሎች ተፈጻሚ የሚሆኑት መቼ ነው? አገልግሎታቸው የሚቋረጠው መቼ ነው?
እነዚህ ውሎች ተፈጻሚ የሚሆኑት መለያ በሚፈጥሩ ጊዜ፣ መተግበሪያን በሚያወርዱ ጊዜ ወይም (በክፍል 2 ላይ ከተጠቀሰው በስተቀር) እነዚህ ውሎች የተያያዙባቸው ማንኛውንም አገልግሎቶች ሲጠቀሙ ነው። እነዚህ ውሎች በእርስዎ ወይም በኮካ ኮላ እስኪቋረጡ ድረስ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
አገልግሎቶቹን በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ምክንያት መጠቀም ማቆም ይችላሉ። መለያዎን ማጥፋት ከፈለጉ፣ እባክዎ በክፍል 15 የቀረበውን የአድራሻ መረጃ ተጠቅመው ኮካ ኮላን ያነጋግሩ እና/ወይም ማንኛውንም ወይም ሁሉንም መተግበሪያዎች ያስወግዱ።
ከመለያዎ ጋር የተገናኘውን የግል መረጃ ማስተካከል ወይም ማጥፋት ከፈለጉ፣ እባክዎ የኮካ ኮላ የደንበኞች የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲን (ወይም ሌላ ለእርስዎ ቅርብ የሆነ የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲን ወይም ማሳሰቢያን) “የእርስዎ ምርጫዎች” ክፍል ይመልከቱ።
አገልግሎቶቹን ለመጠቀም የሚመለከተውን ማንኛውንም ህግ ከጣሱ ኮካ ኮላ ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ወዲያውኑ እና በአፋጣኝ መለያዎን ሊያቋርጥ ይችላል። ኮካ ኮላ አንድ ተጠቃሚ እነዚህን ውሎች በመጣስ አገልግሎቶቹን እየተጠቀመ ነው ብሎ ለማመን ምክንያት ካለው ኮካ ኮላ በማሳወቂያ ወይም ያለማሳወቂያ መለያውን እና አገልግሎቶቹን የማግኘት መብቱን የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደህንነት ጥሰት እንዳለ ካወቅን ወይም ከተጠረጠርን ወይም ኮካ ኮላ ማንኛውንም አገልግሎት መስጠት ወይም መደገፍ ካቆመ ኮካ ኮላ የአገልግሎቶቹን መዳረሻ ሊያግድ፣ መለያዎን ሊሰርዝ ወይም እነዚህን ውሎች ሊያቋርጥ ይችላል። ይህንንም ኮካ ኮላ በራሱ ውሳኔ ሊያደርግ ይችላል።
ማንኛውንም አስፈላጊ የሆነ የተጠቃሚ መረጃ (ህግ በሚፈቅደው መጠን እና በእነዚህ ውሎች መሰረት) መሰብሰብ እንዲችሉ የአገልግሎቶቹን ከማቋረጣችን በፊት ማስጠንቀቂያ ልንሰጥዎ እንሞክራለን። ነገር ግን ተጨባጭ ካልሆነ፣ ህገወጥ ከሆነ፣ ለሌላ ወገን ደህንነት ላይ ጉዳት ካመጣ ወይም ለኮካ ኮላ መብትና ንብረት ጎጂ ከሆነ ላናደርገው እንችላለን።
እነዚህ ውሎች ሲቋረጡ በኮካ ኮላ የተሰጡ መብቶች ያቆማሉ እና ሁሉንም አገልግሎቶቹን መጠቀም ማቆም እና ሁሉንም የመተግበሪያዎች ቅጂዎች ከተንቀሳቃሽ መሣሪያዎ ላይ መሰረዝ አለብዎት።
በባህሪው እነዚህ ውሎች ሲጠናቀቁ ሳይቋረጥ የሚዘልቅ ማንኛውም ድንጋጌ ከተቋረጠ በኋላም ሊቀጥል ይችላል። ለምሳሌ፦ ከታች የተጠቀሱት ሁሉም ድንጋጌዎች ከተቋረጡም በኋላ ይዘልቃሉ፦ በእኛ ተጠያቂነት ላይ ያለ ማንኛውም ገደብ፣ የባለቤትነት ወይም የአዕምሯዊ ንብረት መብቶችን የሚመለከቱ ውሎች፣ የሚከፍሉን ክፍያ ጋር የተያያዘ እና በመካከላችን አለመግባባቶችን በተመለከተ ያሉ ውሎች። መቋረጡ ማንኛውንም የኮካ ኮላን ወይም የእርስዎን መብቶች እና ህጋዊ ጥቅምዎን ወይም ፍትሃዊነት አይገድበውም።
12. ለተያያዙ አገልግሎቶች ተጠያቂው ማን ነው?
አገልግሎቶቻችን በሶስተኛ ወገኖች (የእኛ የሽያጭ ወኪል አጋሮቻችን እና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ጨምሮ)፣ የሶስተኛ ወገን የመልዕክት አገልግሎቶችን (ለምሳሌ፦ Whats App) እና በማስታወቂያዎች (በጋራ የተገናኙ አገልግሎቶች) ያካትታሉ። ኮካ ኮላ ምንም እንኳን አንዳንድ የተገናኙ አገልግሎቶች መረጃዎን ወደ እነርሱ እንዲልኩ ቢፈቅዱም (ለምሳሌ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሉ የ "ላይክ" ወይም "ሼር" ክፍሎች) ኮካ ኮላ የተገናኙ አገልግሎቶችን ሊቆጣጠር አይችልም እንዲሁም አይቆጣጠርም። እባክዎ ለሁሉም የተገናኙ አገልግሎቶች የግል መረጃ ጥበቃ ፖሊሲዎችን እና ሌሎች የአጠቃቀም ውሎችን በጥንቃቄ ይመልከቱ። ማናቸውንም የተገናኙ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከወሰኑ፣ ሙሉ በሙሉ በራስዎ ኃላፊነት እና በተገናኙ አገልግሎቶች ላይ ተፈፃሚ ለሚሆኑ ውሎች እና መመሪያዎች ተገዢ ይሆናሉ እንጂ ለእነዚህ ውሎች ተገዢ አይገዙም።
አገልግሎቶቹ በአጠቃላይ በክፍት ምንጭ ወይም በተመሳሳይ ፍቃዶች (የሶስተኛ ወገን ሶፍትዌር) በነጻ የሚገኙ የሶስተኛ ወገን ሶፍትዌሮችን ሊያካትቱ ይችላሉ። ምንም እንኳን ለእርስዎ የተሰጡ አገልግሎቶች ለእነዚህ ውሎች ተገዢ ቢሆኑም፣ በአገልግሎቶቹ ውስጥ የተካተተው የሶስተኛ ወገን ሶፍትዌር ለሌሎች ፍቃዶች ወይም የአጠቃቀም ውሎች ተገዢ ሊሆን ይችላል፣ ይህም እንደ አስፈላጊነቱ ለእርስዎ ይቀርባል።
13 የኮካ ኮላ ተጠያቂነት በእነዚህ ውሎች ውስጥ የሚገደበው እንዴት ነው?
የኮካ ኮላ የዋስትናዎች ማስተባበያ
በሚመለከተው ህግ የተፈቀደላቸው ከሆነ አገልግሎቶቹ የሚቀርቡት “ባሉበት ሁኔታ” እና ከሁሉም ስህተቶች እና ጉድለቶች እና ከምንም አይነት ዋስትና ውጭ ነው።
የሚመለከተው ህግ እስከሚፈቅደው ከፍተኛ መጠን ድረስ፣ ኮካ ኮላ፣ በራሱ ምትክ እና በተባባሪዎቹ ምትክ፣ እና የእነሱ እና የእነሱ ፍቃድ ሰጪዎች እና ይዘቶች እና አቅራቢዎች (በአጠቃላይ፣ ኮካ ኮላ አካላት) በህግ ወይም በሌላ መልኩ አገልግሎቶቹን በማክበር ሁሉንም የተዘዋዋሪ የሸቀጣሸቀጥ ዋስትናዎች፣ ለተለየ ዓላማ ብቁነት፣ ባለቤትነት እና ያለመብት ጥሰት፣ እና የፍርድ ቤት አጠቃቀምን ዋስትናዎች ጨምሮ በግልጽ ያስተባብላል። ከላይ በተጠቀሰው ሳይገደቡ፣ የትኛውም የኮካ ኮላ አካላት ምንም አይነት ዋስትና ወይም ስምምነት አይሰጡም ወይም አገልግሎቶቹ ፍላጎቶች እንደሚያሟላ የማንኛውም አይነት ውክልና አይሰጡም፣ ማንኛውም የታሰበ እና ሊፈፀም የሚችል ሌላ ተግባር፣ ተመሳሳይ መሆን ወይም ከሌላ ሶፍትዌር፣ ሲስተም ወይም አገልግሎት ጋር መስራት፣ ያለማቋረጥ መስራት፣ የአፈጻጸም ወይም የአስተማማኝነት ደረጃዎችን ያሟሉ ወይም ከስህተት የፀዱ፣ ወይም ማንኛውም ስህተት ወይም ጉድለት ሊታረም ወይም ሊስተካከል ይችላል።
አንዳንድ ህጋዊ ግዛቶች ዋስትናዎች ላይ ገደቦች እንዲጣል፣ ወይም ገደቦች እንዲጣሉ ማመላከት ወይም የሸማቾችን ህጋዊ መብት መገደብን አይፈቅዱም። ስለዚህም አንድአንዶቹ ወይም ሁሉም ገደቦች እርስዎ ላይ ላይጸኑ ይችላሉ።
በኮካ ኮላ ተጠያቂነት ላይ ያሉ ገደቦች
ኮካ ኮላ በእነዚህ ውሎች በተደነገገው መሰረት በኮካ ኮላ ሊለካ በሚችል ሁኔታ ለሚደርሰው ምክንያታዊ ቀጥተኛ እና ሊታዩ ለሚችሉ ጉዳቶች ተጠያቂ ነው።
የሚመለከተው ህግ እስከሚፈቅደው ከፍተኛ መጠን ድረስ፣ ኮካ ኮላ ከታች ለተጠቀሱት ጉዳዮች ተጠያቂ አይደለም እንዲሁም ተጠያቂ አይሆንም፦
- በስምምነት ጥሰት ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳቶችን ጨምሮ ሊገመቱ የማይችሉ ጉዳቶች።
- የማስተማሪያ ወይም የሚያስቀጡ ጉዳቶች።
- ከአገልግሎቶቹ አጠቃቀምዎ ጋር በተያያዘ ማንኛውም የትርፍ ኪሳራ፣ የንግድ ኪሳራ፣ የውል መበላሸት፣ የንግድ ሥራ መስተጓጎል፣ ለወደፊት የታሰበ ቁጠባ፣ የወደፊት የቢዝነስ እድል ማጣት።
- አገልግሎቶቹን በመድረስ የተገኙ ቫይረሶች ወይም ሌሎች ተንኮል አዘል ሶፍትዌሮች በአገልግሎቶቹ ውስጥ ያሉ ስህተቶች፣ ብልሽቶች፣ መዘግየቶች ወይም መስተጓጎል
- ሙሉ አገልግሎቶችን መጠቀም ወይም መጠቀም አለመቻልን ጨምሮ ከማንኛውም ሶስተኛ ወገን ድርጊት ጋር የተያያዙ ኪሳራዎች።
በሚመለከተው ህግ በግልጽ ከተጠየቀው በስተቀር፣ በምንም አይነት ሁኔታ የኮካ ኮላ አካሎች በእርስዎ ላይ የሚኖረው የይገባኛል ጥያቄ ወይም አገልግሎቶቹን ለመጠቀም ወይም በሌላ መንገድ ለመጠቀም አለመቻልን በተመለከተ ለሚነሱት ሁሉም ጥያቄዎች በእነዚህ ውሎችም ቢሆን፣ በስምምነትም ቢሆን ወይም በድምሩ መቶ የአሜሪካ ዶላር (100.00 ዶላር) የሚበልጥ ከሆነሙሉ በመሉ ተጠያቂ አይሆኑም።
እነዚህ ውሎች በእኛ ቸልተኝነት ወይም በተጭበረበረ ስራ ወይም ሌላ ሆን ተብሎ የተደረገን ድርጊት ህገ ወጥ ተግባርን፣ ወይም ለሞት ወይም ለግል ጉዳት የሚያደርስ ተግባርን ከተጠያቂነትን ለማውጣት ወይም ለመገደብ ታስቦ አልተዘጋጀም። ከላይ ከተጠቀሱት ገደቦች ውስጥ አንዳቸውም ልክ ያልሆኑ ሆነው ከተገኙ የኮካ ኮላ አካሎች ለሁሉም ጉዳቶች፣ ኪሳራዎች ወይም የችግር መንስኤዎች ከተጠያቂነት ይገድባቸዋል።
ሸማች እንደመሆንዎ፣ እርስዎ በሚኖሩበት ከማንኛውም የሕግ አካል በሚወጡ አስገዳጅ ህጎች ተጠቃሚ ይሆናሉ። እንደ ሸማች፣ በእነዚህ ውሎች ውስጥ በአካባቢዎ ወዳሉ የህግ ድንጋጌዎች የሚያስኬድዎና የእርስዎን መብቶች የሚጎዱ ነገሮች የሉም።
14. ኮካ ኮላ ከሸማቾች ጋር እንዴት ይገናኛል?
አገልግሎቶቹን ሲጠቀሙ ወይም ኢሜይሎችን ሲልኩ ከእኛ ጋር በኤሌክትሮኒክ መንገድ እየተገናኙ ነው። እንደ ምርጫዎ እና የመለያ ቅንብሮችዎ በተለያዩ የኤሌክትሮኒክ መንገድ ለምሳሌ፦ በኢሜይል፣ በጽሁፍ መልዕክት ወይም በአፕ ፑሽ ማሳወቂያ ወይም በመተግበሪያው ውስጥ መልዕክት በመለጠፍ ወይም በሌላ መንገድ በአገልግሎቶቹ በኩል ከእርስዎ ጋር እንገናኛለን። ከእነዚህ ተግባቦቶች ውስጥ አንዳንዶቹ አውቶማቲክ ሲሆኑ አንዳንዶቹ እንደነበሩ ይላካሉ። አንዳንድ የተግባቦት ዓይነቶችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልንጨምር ወይም ልናስወግድ እንችላለን። በመለያ ቅንብሮችዎ ውስጥ የተወሰኑ የኤሌክትሮኒክስ ተግባቦቶችን ይቀበሉ እንደሆነ ማስተካከል ይችላሉ። ምንም እንኳን የተወሰኑ ተግባቦቶችን ማቆም ቢችሉም አንዳንድ የአገልግሎቶቹን ክፍሎች ለእርስዎ ለማቅረብ ለምሳሌ፦ እንደ የደህንነት ክፍተቶች ማሳወቅ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን እንደ አስፈላጊነቱ ልንልክልዎ እንችላለን።
እርስዎ